'አገልፋኖ' ማለት አገልግል እና ፋኖስ ማለት ሲሆን። እኛ ሰዎች የተፈጠርነው እንደአገልግል ለሌሎች ሰዎች ውስጣችን ውስጥ ያለውን የመልካምነት ስንቅ በማጋራት እንደፋኖስም ለሰው ልጆች ሁሉ የቀናነት ብርሃናችንን አብርተን የሚል ፍልስፍናን አራማጅና ዳግም የሚሰሩበት የሕይወት ማንቂያ መፅሐፍ ደራሲው ከፈለኝ ዘለለው ይባላል። የ "ሐዋዝ" በጎ ሀሳብ ማጋሪያ ምሽት ዋና አዘጋጅ ሲሆን በተጨማሪም የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ ነው። ደራሲው ከዚህ በፊት "የሻማ ብርሃን" እና "አሞዛ" የተሰኙ ሌሎች ሁለት የአዕምሮ ማጎልመሻ መፅሐፍትን በአማርኛና በእንግሊዝኛ ፅፎ ለንባብ በማብቃት ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝቷል። በቅርቡም "ሐዋዝ" የተሰኘ አራተኛ አነቃቂ መፅሐፉን ለአንባቢያን ጀባ ይላል።
New Features added